Unverified

party leaders imprisoned

22:35 Mar 29 2014 Wolayta sodo

Description
የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታሰሩ ዛሬ መጋቢት 20/ 2006 ዓ.ም የወላይታ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሶዶ ውስጥ ስብሰባ ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ በነበረበት ወቅት ፖሊስ ምንም አይነት ምክንያት ሳይሰጥ ሰብስቦ እንዳሰራቸው ከአካባቢው የፓርቲው ተወካዮች ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት አመራሮቹ ድል በትግል በተባለው የፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም እስር ላይ ከሚገኙት መካከልም፡- 1. ወጨፎ ሳዳሞ የወላይታ ዞን ምክትል ሰብሳቢ 2. ታደመ ፍቃዱ የወላይታ ዞን አደረጃጀት ጉዳይ ኃላፊ 3. አቶ ጻድቁ ወ/ስላሴ የወላይታ ዞን የፋይናንስ ኃላፊ 4. አቶ ቴዎድሮስ ጌታ የዞኑ የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ 5. ቦጋለ የፓርቲው አባል ይገኙበታል እነዚህ አመራሮች መታሰራቸውን ተከትሎ የዞኑ የፓርቲው ሌሎች አመራሮችና አባላት ድል በትግል ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ታሳሪዎችን ለመጠየቅም ሆነ የታሰሩበትን ምክንያት ለማጣራት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ መቅረቱን ማወቅ ተችሏል፡፡ ጠዋት 4 ሰዓት ላይ የታሰሩት የዞኑ አመራሮች ምግብ፣ ውሃና ልብስ እንዳይገባላቸው መከልከሉንም የአካባቢው አመራሮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Credibility: UP DOWN 0
Leave a Comment
Name:
Email:
Comments:
Security Code:
14 + 2 =

Additional Reports

Student unrest

17:44 Dec 03, 2010

Mīzan Teferī, 240.87 Kms

UDJ leaders abducted

11:57 Jan 24, 2015

Addis Ababa, Ethiopia, 262.76 Kms

journalist incarcerated

10:28 Feb 10, 2013

Addis Ababa, Ethiopia, 264.92 Kms

Student unrest

17:40 Dec 03, 2010

Addis Ababa, 265.15 Kms

Semayawi memebers abducted.

12:04 May 12, 2015

Addis Ababa, 265.15 Kms